
እኔው ከራሴ ከምክሬ
ከተቀዳው ክሬ
ደጅ ስጠና ስሞግት
ያልተሰነዘረ ጡጫ ስመክት
ጥላ ስመትር ስበልት
እኔው ከራሴ በራሴ
ተነክሼ በገዛ ጥሬሴ
ተቀፍድጄ በጨለማ ተቆልፌ
ውስጥ ዕርቃኔን ተገፍፌ
ጀርባ ሰርጤን ተገርፌ
ስደናበር እየደጋገምኩ
የአንጎሌን ክር እያዳመጥኩ
ጥልመት ለብሼ
አይቀሬ ነው ማነከሴ
ተከስሼ
ከተቀዳው ክሬ. 2010 ዓ.ም
ከዶ/ር ሳሙኤል ወልዴ “መነጋገር” ከተሰኘው መጽሐፍ ገጽ 48 የተወሰደ