ከመደነጋገር መነጋገር
A Key to Promote Success among Family Members, Community Members, Ethnic Groups, and the Larger Ethiopian Society.
About the book
ቤተሰባዊ፣ ማኅበረሰባዊ፣ ብሔረሰባዊና ኅብረተሰባዊ ዙሪያ ገጠም ውጤታማነት መክፈቻ Communication to Reduce
Confusion: A Key to Promote Success among Family Members,
Community Members, Ethnic Groups, and the
Larger Ethiopian Society.
የመጽሐፉ ዓላማ
ቤተሰባዊ፣ ማኅበረሰባዊ፣ ብሔረሰባዊና ኅብረተሰባዊ ዙሪያ ገጠም ውጤታማነት መክፈቻ Communication to Reduce Confusion: A Key to Promote Success among Family Members, Community Members, Ethnic Groups, and the Larger Ethiopian Society.
ስለ ጸሐፊው
Dr. Samuel Wolde is an Ethiopian Licensed Clinical Neuropsychologist (LP) with intensive clinical experiences, including working as mental health and addiction lead therapist in a psychiatric hospital for more than eight years. Since the year of 2003, following his advanced graduate education in a Clinical Psychology and Applied Psychology, Dr. Wolde has been engaged in providing direct psychotherapeutic care for individuals, families, and groups both in Arizona and Colorado. Dr. Wolde’s work includes collaboration with the State of Arizona correctional facilities and Federal Bureau of Prison to provide mental health services for inmate populations. As a psychometrician, diagnostician, licensed clinical psychologist and provider, team leader, program manager, program developer for an inpatient psychiatric hospital, and clinical supervisor for graduate level Counseling and Social Work students, Dr. Wolde has demonstrated excellent work ethics and contributed greatly to wellness of diverse communities in Arizona.
Dr. Wolde is currently associated as a neuropsychologist/clinical psychologist consultant with an agency in the East-coast devoted to treat individuals facing various cognitive difficulties, including Traumatic Brain Injury (TBI), Mild Cognitive Impairment (MCI), Alzheimer, Cardio Vascular Dementia, substance induced psychosis, and general psychiatric presentations. Additionally, Dr. Samuel Wolde, due to a long standing passion of equipping new generations of clinicians, has been involved extensively in the work of academia. For the last 12 years , Dr. Wolde’s academic commitment includes educating undergraduate psychology students at Arizona Christian University and University of Phoenix. Furthermore, Dr. Wolde is currently an associate professor at Grand Canyon University, School of Graduate Clinical Studies.
Dr. Wolde holds multiple independent licenses, including Licensed Professional Counselor (LPC) and Licensed Independent Substance Abuse Counselor (LISAC). Dr. Wolde completed his undergraduate degree in Communications from Colorado Christian University. Dr. Wolde holds several graduate degrees in Master of Clinical Counseling and Master of Divinity emphasis in Leadership and Ancient Biblical Languages, Master of Applied Psychology from Walden University. Dr. Wolde holds Ph.D in Clinical Psychology from Denver University/Walden University.
መጽሐፉ የሚሸጥባቸው ቦታዎች
Jafar Book Store Addis Ababa Ethiopia +251911125324 https://www.jaferbooks.com/
Mekane Yesus Church
Meserete Kirstos Church
መጽሐፉ ሲገመገም
“ከመደነጋገር መነጋገር”
በመስከረም አበባ አበረ እይታ
በጥፋት መሰረት ታንፀው በደምሳሳ እይታ የተነሳሱ ጥቂት ያለአግባብ የታጠቁ የውድመት መልዕከተኞች የማይታሰብ ሰቆቃና ዕልቂት በትውልድ ላይ እንደዝናብ ያዘንባሉ፡፡ ከተሞችንና የልማት ተቋማትን ያጋያሉ፡፡ እነዚህ በዕውር ድንብር የተቃኙ የመከራ ሰለባ እሳት ለመቆስቆስ የተሰማሩ አጥፊዎች የክፍለዘመናትና የብዙ ትውልዶች አሻራ ያረፈባቸውን ዘመን ጠገብ የስልጣኔና የዕድገት ውጤቶች ከመቅፅበት ወደ ብዙ አመታት ጨለማ የኋልዮሽ ይመልሳሉ፡፡ አውዳሚ ለመሆን ክህሎት አይጠይቅም፡፡ የማምለኪያ ቦታዎች ፣ ትምህርት ቤቶች፣ ሆስፒታሎችና የመሳሰሉ ለግንባታ አመታትን ያስቆጠሩ የብዙሃን መገልገያ ተቋማትን ዶግአመድ ለማልበስ ጊዜና ስልጠና አያስፈልገውም፡፡ የሚያስፈልገው በክፋትና በበቀል ስሜት የተለከፈ አፍላነት ነው፡፡ ያለዕውቀት የተለቀቀ አፍላነት እሳት ነው፡፡ በጥንቃቄ ያልተገራ ስሜታዊ ግልቢያ ያገኘውን ታሪካዊ ዳርቻ የሚሰለቅጥ፣ የአሁኑን የሚደመስስ፣ መጪውን የሚያጨልም ነው፡፡ ከምክንያታዊነት የተፋታ በጭፍን የሚነዳ የስሜት ግነፈላ ሃዲዱን ስቶ በተሳሳተ መስመር እየከነፈ ያገኘውን ሁሉ ያለምህረት እያጠፋና እየጨፈላለቀ በመጨረሻም እራሱ በፈጠረው እሳት ተቀጣጥሎና ጋይቶ እንደሚወድም ባቡር ነው፡፡ በስህተት ተግባር ላይ ተሰማርተው ልማትን እንደማይጠብቁ ሁሉ በሰናይ ዓላማ ስር ተጠልለው የጥፋትን ሰይፍ አይመዙም፡፡
ሰዎች ከምክንያታዊነት በተፋታ መንገድ የሚወስኑት ውሳኔ እንዲሁም በስሜትና ግልፍተኝነት የሚፈጽሙት ተግባር መቼም ቢሆን የማይቀለብሱትን ውድመትና የእድሜ ልክ ጸጸትን ያወርሳቸዋል። ነገር ግን እነዚህን ድርጊቶች የወለዱ እኩይ እሳቤዎች አሁን ተዘርተው አሁን የበቀሉ ዘሮች ናቸው? ለብዙ ዘመናት ተዋዶ፣ ተዋልዶ፣ ተከባብሮና ተሳስቦ በኖረ ህዝብ መሀል ይህ አስከፊ ተግባር በዚህ መጠንና ቅፅበት እንዴት ተፈፀመ? ብሎ ለጠየቀና ለመልሱ ግራ ለተጋባ እንዲሁም ስሜት ከምክንያታዊነት ፍፁም ሲፋታ ምን ሊሆን ይችላል? መሰል ጥፋቶችንስ በእርግጥ ያስከትላል? መውጪያ መንገዱና መፍትሔውስ? እያለ በብርቱ ለሚጠይቅ ባለአዕምሮ፣ የወንጌል ብርሀን በበራላቸው የስነአእምሮ፣ ስነልቦናና፣ ስነመለኮት ምሁሩ በሆኑት በዶክተር ሳሙኤል ወልዴ ተደርሶ የቀረበው “ከመደነጋገር መነጋገር” የሚለው ግሩም ፣ ወቅታዊና ሳይንሳዊ መጽሐፍ መልስ ነው። ትውልድን እየበሉ፣ አገርን እያወደሙ ፣ እናቶችን እያስለቀሱ፣ የአገር መሪዎችን፣ ተፎካካሪ ፖለቲከኞችን፣ የሐይማኖት አባቶችንና ምሁራንን ግራ እያጋቡ ላሉ አገር አቀፍ ተግዳሮቷች መፍትሄው “ከመደነጋገር መነጋገር ከመነካከስ መወቃቀስ” መሆኑን በማሳየት አንባቢያን ለመነጋገር ክህሎት እንዲነሳሱ፣ በብርቱና በጥበብ ደራሲው ይቀሰቅሳሉ።
“ከመደነጋገር መነጋገር” የሚለውን የመጽሀፉን ዕርስ ተመልክቶ እንደኔ የመነጋገርን አስፈላጊነት የማይረዳ ሰው በአገራችን አለን? ኢትዮጵያስ ውስጥ እስከዛሬ በመነጋገር የተፈታና የሚፈታ አገራዊ ችግር ይኖራል ወይ? ብሎ በዙሪያው በሚያየውና በሚሰማው ሁሉ ግራ በመጋባትና በመቆዘም ጥያቄ ለሚጠይቅ አንባቢ ደራሲው በመፅሐፋቸው አዎ! አለ ይላሉ። በመነጋገር ክህሎት በተሞላና “በእውነት ላይ ተመስርቶ በፍቅር በተሟሸ” የልብ ለልብ ምክክር የማይፈቱ ቤተሰባዊ፣ ማህበረሰባዊ፣ ህብረተሰባዊና አገራዊ ችግሮችና የማንሻገራቸው እንቅፋቶች የሉም በማለት አብሮና ተከባብሮ የመኖር ተስፋችንን እነደገና ይቀሰቅሳሉ። አስገራሚ ታሪካዊ እውነቶችንም በምሳሌነት በማንሳት አልረፈደብንም ይላሉ።
አሁን አሁን በእኛ የእርስበዕርስ እልቂት የሚገረሙትና ምናልባትም ከመጋረጃ ጀርባ የሚሳለቁብን የበለፀጉት ምዕራባዊያን አገሮች ከጥቂት አስርት አመታት በፊት በስሜታዊነትና በግብታዊነት ተነሳስተው የሌላ አገር ድንበር ጥሶ በገባ ውሻ ጦሰ ሰበብ እንኳን ሳይቀር አንዱ አገር በሌላው ላይ የጦርነት ክተት አውጀዋል። ጦር ሰብቀውና አዝምተው ተፋጅተዋል። ተላልቀዋል በማለት የታሪክን መዛግብት ገልፀው ያሳዩናል። የተጠቀሰውንና ሌሎችንም አስቂኝና አስገራሚ ምዕራፍ አልፈው ምዕራባዊያኖቹ ለአሁኑ የሰከነ ፖለቲካቸውና ለደረሱበት ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ብልፅግና ዋና ሃዲዱ ተቀራርቦ የልብ ለልብ መነጋገራቸው ብቻ ነው በማለትም ሃሳባቸውን ያስረግጣሉ።
ለግል ጥቅማቸው ያሰፈሰፉ በመሀል ያሉ ‘ጆከሮችን’ ፣ አንቂዎች ነን ባዮችንና የግጭት አትራፊዎችን ከመሃል በማስወገድ “በእውነት ላይ ተመስርቶ በፍቅር በተሟሸ” ውጤታማ ንግግር የጋራ አላማን ማስጠበቅ፣ የጋራ ግንዛቤ መፍጠር፣ ጥርጣሬና ሀሜትም በማጥፋት ወደጋራ ግብ መጎዝ እንደሚቻል በግልፅ ያመላክታሉ። ለዚህም እንዲረዳ ሳይንሳዊ ትንታኔና አጋዠ መርሆችን ለአንባቢው በዝርዝር ያስቀመጡበትም መንገድ ልዩ ነው። “ዝምታ ወርቅ ነው” “ሙያ በልብ ነው” እያለ የነበረውን ትውልድም ሆነ “አሁን ግዜዬ” ነው ብሎ ዘመኑ ባስገኘለት የመናገሪያ መንገድ ሁሉ በየአደባባዩ ለሚዘላብደው ትውልድ ከውጤታም የንግግር ክህሎት መጉደላቸውን በማስረጃ ያሳያሉ። አንዳንዴም በእውቀት በመገሰፅ ሁሉንም ዜጋ ወደ ትክክለኛው ሀዲድ ለመመለስ ይታገላሉ። ሁላችንም እንደምንረዳው ዛሬ የነገው ስኬት መሰረት የሚታነጽበት አጋጣሚ ነው። አንዱና ዋነኛው የአገራዊ ብልፅግና መሰረት ደግሞ ደራሲው እንዳሰመሩበት “ጭንብልን አውልቆ” ልብ ለልብ ተቀራርቦ የመነጋገርና ችግርን በንግግር የመፍታት ክህሎት ነው።
በእርግጥ መነጋገር ለችግሮቻችን መፍትሄን የሚያመጣ ከሆነ በአገራችን የሚከሰቱት ግጭቶች ለምን እልቂትን ያዘንባሉ? ስላልተነጋገርን ነው? ወይስ መናገራችንን እንደመነጋገር እየቆጠርን ሰንብተን ነው?
ቤተሰብና የህብረተሰብ አካላት በተወለዱበት አገርና በሚኖርበት መንደር ውስጥ የሚገኘውን የተፈጥሮ ፀጋና የተለያዩ አቅራቦቶች እየተቋደስ ሲኖሩ ሁል ግዜ በመከባበርና በመተሳሰብ ነው የሚኖሩት ብለን ብንል ራሳችንን መዋሸት ነው። በሚሰማንም አድማጭ ዘንድ ትዝብት ላይ እንወድቃለን። ግጭት የአቅርቦት እጥረት ባለባቸው ቦታዎች ላይ እለት በእለት ሲፈጠር የምናስተውለው ጉዳይ ነው። “ከመደነጋገር መነጋገር” በቤተሰብ፣ በማሕበረሰብና በብሔረሰቦች መካከል በተደጋጋሚ በሚከሰቱ ግጭቶችና በሚያስከትሏቸው ውድመቶች ግራ ለተጋቡ አንባብያን የተስፋን ጭላንጭል በሚያሳይ መንገድ የግጭትን መንስኤና መፍቻ መንገዶችን በግሩም ሁኔታም ተተንትኖበታል። ለችግሮቻችንም እነደ ዓይነተኛ የመድሃኒት “ማዘዣ ቀላጤ” (prescription) በግሩም ሁኔታ ለመለወጥ ለተዘጋጀ በለአዕምሮ ዜጋ ሁለ ታዟዋል።
“ግጭቶች የአስተሳሰባችንን አድማስ እንድናሰፋ የሚጠቅመን መነፅርና ወደ ማደግና ወደ መሻሻል የሚያስተናብሩ አጋጣሚዎችና ጓህ ቀዳጆች ናቸው” “ግጭት አብሮ የመኖር ጠላት ሳይሆን ነዋሪዎች አብረው ለመኖር የሚከፍሉትን የዋጋ መጠን የሚለኩበት ሚዛን ነው” በማለት ዶክተር ሳሙኤል በእያንዳንዱን ግለሰብ ትከሻ ላይ የሀላፊነቱ ድረሻ ሲያሳርፉ፣ ለመሪዎችም “በቤተሰብና በማህበረሰብ፣ በብሔረሰብና በህብረተሰብ መካከል ግጭት ሲፈጠር ለመሪዎች የሚደወል የተግባር ጥሪ ነው” “ችግርና አለመግባባት ለእድገት በር ከፋች አጋጣሚ ብቻ ሳይሆን እውነተኛ መሪዎች ራሳቸውን የሚገልጡበት ነባራዊ መድረክ ነው” በማለት በየደረጃው በአገራችን የመሪነት ሀላፊነት ላይ ያሉ ሁሉ እራሳቸውን እንዲፈትሹና ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ ያስገነዝባሉ።
“ከመደነጋገር መነጋገር” የስነፁህፍ ውበትን ተላብሶ በስምንት ምዕራፎች ተሰድሮ በርዕሰ ጉዳዩ ላይ የጠለቁ ሳይንሳዊ ትንተነዎች፣ ወቅታዊ ኩነቶች፣ ሚዛናዊ ስነመለኮታዊ መረዳቶች እንዲሁም ታሪካዊ ክስተቶች ተዋህደው የቀረቡበት መፅሀፍ ነው። በእያንዳንዱ ምዕራፍ ብቻ ሳይሆን በሁሉም አንቀፅ በሚባል ደረጃ የሚያመራምሩ፣ የሚያነቁና ወደከፍታ የሚያሻግሩ ሀሳቦች ተሰድረዋል። እኔ ግን በዚህች አጠር ያለች ፅሁፍ ሁሉንም ምዕራፎች በመነካካት እይታዬን በማካፈል ፋንታ ግጭቶቹ ላይ መቆየቴ ግን ከሰሞኑ ልቤን ካከበደው ክስተት ጋር ንባቤ ስለገጠመብኝና በመፅሀፉ ውስጥ ለወቅታው ችግሮቻችን ብዙ መደሀኒትና ተስፋ የሚሆኑን እውነቶች ሰለተመለከትኩኝ ነው።
ከመደነጋገር መነጋገር መሳጭ፣ ገላጭ፣ ሞጋች፣ አስተማሪና አነቃቂ በሆነ መንገድ የቀረበ እጅግ በጣም የተመሰጥኩበትና ብዙ የተማርኩበት መፅሀፍ ነው። በኔ መመዘኛ በዚህ ደረጃና ዕርስ ተዘጋጅቶ ያነበብኩት በአማርኛ ቋንቋ የተፃፈ መፅሀፍ የለም ብል ማጋነን አይሆንብኝም። ይህን አስረግጬ ያለምንም ማመንታ ይህን ፁሁፍ ለምታነቡ የምገልፀው መፅሃፉን ስታነቡት በአስተያየቴ እንደምትስማሙ በማመንና ከዚህ በጥራትና በጥንቃቄ ተሰናድቶ ከቀረበልን ማዕድ እንዳትጎድሉ በመሻትም ጭምር ነው።
የስነአዕምሮ፣ የስነልቦናና የስነመለኮት ምሁርን ዶክተር ሳሙኤል ወልዴን በዚህ አጋጣሚ ስለዚህ በብዙ እውቀት ሰድረው በጥንቃቄ አሰናድተው ስላቀረቡልን መፅሀፍ ከልቤ አመሰግናለውኝ። በሌሎችም ሳይንሳዊ፣ አስተዳደራዊ፣ አገራዊና ቤተክርስቲያናው ጉዳዮች ላይ መሰል ሚዛናዊና በሳል መፃህፍቶቻቸውን ለማንበብ መጎጎቴን አልሸሽግም። ሳይዘገዩ ጀባ እነደሚሉን ተስፋ አደርጋለው። መፅሀፉን የምታነቡ አንባቢዎችም ከምንባባችው መልስ ተመሳሳይ ጥያቄ እንደኔው ታቀርቡ ይሆናል ብዬ እገምታለው። አስተያየታችሁንም በዚሁ መድረክ ለመስማትና አገራዊ ፋይዳ ባላቸው በመፅሀፉ ውስጥ በተነሱ ጭብጦች ዙሪያ ለመወያየት እንድንችል የዚህ ድህረ ገፅ አጋፋሪ ሁኔታዎችን ቢያመቻቹልን መልካም ይሆናል እላለው። ጥያቄዬንም ለድህረ ገጹ አጋፋሪና አጋሮቻቸው በትህትና አቀርባለው። በቸር እንሰንብት!
የመስከረም አበባ አበረ
ymeskerema@gmail.com
መታሰቢያነቱ


