about
About Us
ዓላማ
የዚህ ማኅበራዊ ድረ-ገጽ ጽንሱም ውልደቱም ከወገን ጋር የተገኘን በጎ እውቀት ለመከፋፈል ካለ የመለካም ፈቃደኝነትና ጉጉት የፈለቀ ነው። በዚህ ማኅበራዊ ድረ-ገጽ ትኩረት ተሰጥቷቸው ከሚዳሰሱስት ንዑሥ የእወቀት ዘርፎች መካከል የሥነ-ልቦና ጥቃት እንዲሁም ከአዕምሮ ጤና አኳያ የሚነሱ ጉዳዮች ዋነኞቹ ናቸው። የአዕምሮና የሥነ-ልቦና ጥቃትን “በፈጣሪ ከመቀሰፍ” ካልሆነም “በጋኔን ከመለከፍ” ጋር ብቻ በማያያዝ በሰንሰለት ታስረው የሚማቅቁትንና በጨለማ ክፍል ተቆልፈው የሰው ዓይን እንዳያቸውና የፀሃይ ብርሃን እንዳያጋኛቸው የተፈረደባቸውን ተጠቂዎች ቤት ይቁጠረው። ከዚያም ባለፈ፣ ኢትዮጲያዊያን የአዕምሮ ሕመምና የሥነ-ልቦና ጥቃት ሰለባ ሊሆኑ እንደማይችሉ ሁሉ በነዚህ የጤና ቀውሶች ዙሪያ ያለው ዝምታ ጆሮ ጭው ያደርጋል።
በምድረ-ኢትዮጲያ ያለው አብዛኛው ሕዝብ ሆነ በተላለዩ የዓለም ክፍላት የተበተነው ኢትዮጲያዊ ደፍሮ በአደባባይ አንስቶ ከማይነጋገርባቸው ርዕሶች መካከል በሥነ-ልቦና እንዲሁም በአዕምሮ ሕመም ዙሪያ የሚከሰቱ ተግዳሮቶችን ነው። የራሳቸውን ሕይወት የሚያጠፉ፣ በዕፅ ሱስ ባርነት ተቀፍድደው የሚጎሳቆሉ፣ ተገቢውን የሥነ-ልቦናና የአዕምሮ ሕክምና ባለማግኘት ምክንያት የሚማቁ ወገኖችን ጩኸትና የሞታቸውን መርዶ መስማት እየተለመደ የመጣ አሳዛኝ ቤተሰባዊ፣ማኅበረሰባዊ እንዲሁም ሃገራዊ ሃቅ ነው። ይህ ማኅበረሰባዊ ድረ-ገጽ በማኅበረሰቡ ዘንድ ጎልተው የሚታዩትን የሥነ-ልቦና ቀውሶች ነቅሶ በማውጣት የመግቢያ ሙያዊ ፅሑፎችን በማዛጋጀት፣ በሙያው ላይ የደረጁ አዋቂዎችንም በመጋበዝ ግንዛቤዎችን ለማስርፅ አስተዋፅዎ ያዳረጋል። የውይይት መድረኮችንም በመክፈት በተሳፊዎች መካከል በምክንያናዊነትና በመከባበር ላይ የተመሠረተ የሃሳብ ማሻኮት እንዲኪያሄድ ያስተናብራል። በተጨማሪም ከአንባቢዎችና ከተሳታፊችዎች በሥነ-ልቦና ጉዳዮች ዙሪያ ለሚነሱ ጥያቂዎች ሙያዊ መልሥ በመለገስ ጠያቂዎችን ትክክለኛ እርዳታ ወደሚያግኙበት ማዕከላት ያመላክታል።
ማስገንዘቢያ፡- ይህ ማኅበራዊ ድረ-ገጽ ለኅበረተሰቡ ድጋፍ ለመስጠት የተከፈተ መድረክ እንጂ የሕክምና ጣቢያ አይደለም። ይህ ማኅበራዊ ድረ-ገጽ በሥነ-ልቦና እንዲሁም በአዕምሮ ሕመም ላይ ሰልጥነው መንግሥታዊ እውቅና ተስጥቶአቸው የሚያገለጉ ባለሙያዎችን የሕክምና ምክር፣ ሂደት እንዲሁም የሕክምና መርጃ ቀላጤን አይተካም።
ዶ/ር ሳሙኤል ወልዴ
Dr. Samuel Wolde is an Ethiopian Licensed Clinical Neuropsychologist (LP) with intensive clinical experiences, including working as mental health and addiction lead therapist in a psychiatric hospital for more than eight years. Since the year of 2003, following his advanced graduate education in a Clinical Psychology and Applied Psychology, Dr. Wolde has been engaged in providing direct psychotherapeutic care for individuals, families, and groups both in Arizona and Colorado. Dr. Wolde’s work includes collaboration with the State of Arizona correctional facilities and Federal Bureau of Prison to provide mental health services for inmate populations. As a psychometrician, diagnostician, licensed clinical psychologist and provider, team leader, program manager, program developer for an inpatient psychiatric hospital, and clinical supervisor for graduate level Counseling and Social Work students, Dr. Wolde has demonstrated excellent work ethics and contributed greatly to wellness of diverse communities in Arizona.
Dr. Wolde is currently associated as a neuropsychologist/clinical psychologist consultant with an agency in the East-coast devoted to treat individuals facing various cognitive difficulties, including Traumatic Brain Injury (TBI), Mild Cognitive Impairment (MCI), Alzheimer, Cardio Vascular Dementia, substance induced psychosis, and general psychiatric presentations. Additionally, Dr. Samuel Wolde, due to a long standing passion of equipping new generations of clinicians, has been involved extensively in the work of academia. For the last 12 years , Dr. Wolde’s academic commitment includes educating undergraduate psychology students at Arizona Christian University and University of Phoenix. Furthermore, Dr. Wolde is currently an associate professor at Grand Canyon University, School of Graduate Clinical Studies.
Dr. Wolde holds multiple independent licenses, including Licensed Professional Counselor (LPC) and Licensed Independent Substance Abuse Counselor (LISAC). Dr. Wolde completed his undergraduate degree in Communications from Colorado Christian University. Dr. Wolde holds several graduate degrees in Master of Clinical Counseling and Master of Divinity emphasis in Leadership and Ancient Biblical Languages from Denver Seminary and Master of Applied Psychology from Walden University. Dr. Wolde holds Ph.D in Clinical Psychology from Denver University/Walden University.

